የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የተማሪ መሳሪያዎች መመለስ
Posted on: June 21, 2024
Summary: አብዛኞቹ ተማሪዎች የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች መሳሪያቸውን ይመለሳሉ።
የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) የተማሪ መሳሪያዎች የትምህርት አመቱ ከማጠናቀቁ በፊት ወደ ትምህርት ቤትዎ መመለስ አለባቸው።የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች መሳሪያዎ እና መለዋወጫዎች ካልተመለሱ፣መቀጮ ለመክፈል ይጠየቃሉ።
ተማሪዎች መመለስ የሚያስፈልጋቸው የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች መሳሪያዎ እና መለዋወጫዎች
- አብዛኞቹ ተማሪዎች የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች መሳሪያቸውን ይመለሳሉ።
- በመከር ወቅት በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የማይመዘገቡ ተማሪዎች በሙሉ።
- በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የበጋ ትምህርት ፕሮግራሞች የሚማሩ ተማሪዎች ያሁኑን መሳሪያ ይመልሱ እና ለየሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የበጋ የትምህርት ፕሮግራሞች ሌላ መሳሪያ ይሰጣሉ። የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የበጋ ትምህርት ፕሮግራሞች የተራዘመ የትምህርት ዓመት (Extended School Year (ESY)) የማካካሻ አገልግሎቶች (Recovery Services)፣K-8 Summer Staircase፣ወይ Credit Retrieval ያካትታል።
ልዩ ሁኔታዎች፡ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መሳሪያዎችን በበጋው ወቅት ማቆየት የሚችሉ ተማሪዎች
- ተማሪዎ በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አካባቢ የማይስተናገደውን የበጋ ትምህርት ፕሮግራም የሚከታተል ከሆነ (ምሳሌ Upward Bound at Seattle University)
- ማሳሰብያ:የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መሳሪያ በበጋው የትምህርት ፕሮግራም መጨረሻ ላይ ሲመለስ የሚሰረዝ ቅጣት በመለያዎ ላይ ያያሉ።ለዚህ የትምህርት መሳርያ ለመመለስ እባክዎን Student TechLine በ 206-252-0100 ወይም በlaptops@hungrong.comያነጋግሩ።
- ተማሪዎ እንደ የAAMA Student Leadership Council ያሉ የዲስትሪክት የተማሪ አመራር ኮሚቴ አባል ከሆነ።
- ተማሪዎ የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኝ ከሆነ እና የግላዊ የትምህርት ፕሮግራም አካል የሆነ መሳሪያ ካለው።ተማሪዎች በIEPቸው መሰረት ሊጠቀሙበት የሚችሉ በየቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ዲፓርተመንት(Department of Technology Services) እና/ወይም በየልዩ ፍላጎት ትምህርት አጋዥ ቴክኖሎጂ( Special Education Assistive Technology) የተሰጠ መሳርያ (በተለምዶ ደማቅ አረንጓዴ ታግ ያለው።
በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ እንደተገለጸው መሳሪያው ወይም መለዋወጫ ዕቃው ካልተመለሰ በተማሪው መለያ ላይ ቅጣት ይጣልበታል።ትምህርት ቤትዎ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ማናቸውንም መለዋወጫዎች ካላወጣ፣እንዲከፍሉ አይደረጉም።
የሚመለሱ መሣሪያዎች እና መለዋወጫዎች:
- ላፕቶፖች ($350 መቀጮ)፣የላፕቶፕ ቦርሳ ($10.50 መቀጮ)፣እና የላፕቶፕ ቻርጀር ($48 መቀጮ)
- iPads ($250 መቀጮ)፣iPad case ($49 መቀጮ)፣እና iPad charger ($40 መቀጮ)
- WiFi hotspots እና ቻርጀር ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ቅጣቱን (ቹን) በመስመር ላይ በSource Account በኩል መክፈል ይችላሉ።
ቅጣቶቹ በተማሪዎ ትምህርት ቤት ሊከፈሉ ይችላሉ።እባክዎን የተማሪ ቅጣቶችን እንዴት መክፈል እንደሚችሉ ከትምህርት ቤትዎ ጋር ይነጋገሩ።
ስለ የቴክኖሎጂ ክፍያዎች አስመልክቶ በመስከረም 2021 ወር ለቤተሰቦች የተላከውን ደብዳቤ ያንብቡ።
ጥያቄዎች ካሉዎት፣እባክዎን የ Student Techline በ laptops@hungrong.com ወይም በ 206-252-0100 ያናጋግሩ